ስፖርት port ስፖርትን እንመግባለን ረቡዕ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም visit us www.hatricksport.net 6 300ሺህ- የኢንተር ሚላኑ ፕሬዚዳንት ስቴቨን ዛንግ የጣሊያን እግር ኳስ እንዳይካሄድና ጣሊያናዊያንን ከቤታቸው እንዳይወጡ ያስገደደው የኮረና ቫይረስን ለመከላከል ይረዳል በማለት ከ300 ሺህ በላይ የፊት ማስክና ለህክምና የሚውል የመድኃኒት ስጦታ ለሲቪሉ ማህበረሰብ ድጋፍ አድርገዋል፡ ፡ ከ15ሺ ሰዎች በላይ በቫይረሱ የተጠቁባትና ከ1,016 በላይ ሰዎችን በሞት የተነጠቀችው ጣሊያን ከቻይና ቀጥሎ በበሽታው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሀገር ናት፡፡ :- quick kick ፒዬር አሜሪክ ኦባሚያንግ “ለአርሰናል መጫወት ትልቅ ክብር ነው” ዘመን ጋቦናዊው ኢንተርናሽናል ፒዬር አሜሪክ ኦባሚያንግ በያዝነው የውድድር የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከፍተኛ ጎለ አስቆጣሪ ነው፤የወርቅ ጫማውን ለማግኘት በሚደረገው ትግልም ከሌይሲስተር ሲቲ አቻው ጂሚ ቫርዲ ጋር በመሆን ከፊት እየመራ ይገኛል፡፡ ደጋፊዎች በቅርቡ በዩሮፓ ሊግ በኤምሬትሱ የመልስ ጨዋታ ያመከናትን ወሳኝ ኳስ ተከትሎ በጣም በመከፋቱ ከጎኑ መሆናቸውን እያሳዩት ይገኛሉ፡፡ ለአርሰናል መጫወት መቻል ስሜቱ የለየ ነው፤ልጅ እያለሁ የአርሴናልን ጨዋታዎች እከታተል ነበር፤ምክንያቱም ሁልጊዜም ቡድኑ በታላላቅ ተጨዋቾች የተሞላ ነበር፡፡ በርካታ ዋንጫዎችንም አሳክተዋል፡፡ ለእኔም እዚህ በታላላቅ ተጨዋቾች በተሞላ ክለብ ውስጥ መገኘት መቻል ትልቅ ደስታን የሚፈጥርልኝ ነው፤ይህ የእኔ ዕውነተኛው ሰሜቴ ነው፡፡” እዚህ ያሉ ደጋፊዎችን በጣም ነው የምወዳቸው፤በኢንስታግራም ገጼ ከእነሱ ጋር መገናኘት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፤ምክንያቱም ያቺን ኳስ ካመከንኩ በኋላ (ከኦሎምፒያኮስ) ሁሉም ሰው እኛን ዛሬ ገድሎናል ሲል ነበር፤ነገር ግን አብዛኛዎቹ ራስህንና አዕምሮህን አረጋጋ ሲሉኝ ነበር፡፡ ከእነሱ ጋር ሆኜ በዘህ መልኩ መቀጠል በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ ከኦሎምፒያኮስ ጨዋታ በኋላ ወደ ቤቴ ስመለስ ልጆቼ ሳይቀሩ “አትጨነቅ ይህ ነገር የሚከሰት ነው” ብለውኛል፤በዚህም ምክንያት በጣም ደስተኛ ነኝ በጣምም ተፅናንቻለሁ፡፡ በእርግጥ የሆነው ነገር በጣም የሚያም ነበር፡ ፡ ነገር ግን ይህ እግር ኳስ ነው፡፡ ዝግጁ ሁልጊዜም ለመሆን እሞክራለሁ፤ምንም ነገር ቢፈጠር ማለቴ ነው፡፡ ለዛም ነው ያ ነገር ከተፈጠረ በኋላ ራሴን መለስ ብዬ ለመመልከት የፈለኩት፤ለእያንዳንዱ ጨዋታ ሁልጊዜም ዝግጁ መሆን እፈልጋለሁ፤እናም አሁን ላይ ስራዪን በትኩረት በመስራት ላይ እገኛለሁ፡፡ ጋቦናዊው በተጨማሪም በዩሮፓ ሊጉ በአክሮባቲክ መንገድ ኦሎምፒያኮስ ላይ ያስቆጠራት ጎል የየካቲት ወር የደጋፊዎች ምርጧ ጎል በመባል ተመርጣለች፡፡ 22% የደጋፊዎችን ድምፅም ማግኘት ችላለች፡፡ ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር በነበረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ እና መድፈኞቹ በኤምሬትስ 4ለ0 ባሸነፉበት ግጥሚያ ከ35 ቅብብሎሽ በኋላ ሜሱት ኦዚል የስቆጠራት ጎል በ21% ድምፅ ሁለተኛ ስፍራን ማግኘት ችላለች፡፡ እንዲሁም በተጠባባቂው ቡድን ዳንኤል ቫን ዶንካስ ማንቸስተር ሲቲ ላይ ያስቆጠራት ጎል በ17% ድምፅ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፤ፒዬር ኤሜሪክ ኦባሚያንግ በፕሪሚየር ሊጉ የወሩ ኮከብ ተጨዋች ምርጫ ከታጩ ተጨዋቾች መካከልም አንዱ ሆኗል፡፡ የመድፈኞቹ አምበል በየካቲት ወር በሶስት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን በኤምሬትስ ኒውካስትልን ሲገጥሙ ካስቆጠራት አንድ ጎል በተጨማሪ ከካርሎ አንቼሎቲው ኤቨርተን ጋር በነበረው ፈታኝ ጨዋታ የሰሜን ለንደኑ ክለብ 3ለ2 ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል፡፡ ለየካቲት ወር የሊጉ ምርጥ ተጨዋች እጩ ውስጥ የተካተቱ ተጨዋቾች የቼልሲው ማርኮስ አሎንሶ፣ የአሰናሉ ፒየር ኤሜሪክ ኦባሚያንግ፣ የኤቨርተኑን ዶሚኒክ ካልቨርት የዎልቨር ሀምፕተን ወንድረርሱ ማት ይህርቲ፣ የማንቸንሰትር ዩናይትዱ ብሩኖ ፈርናንዴስ እና የበርንሌው ኒክ ፓፕ ናቸው፡፡ ልዊን፣ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በአለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኝ መልክ የተከሰተውን የኮረና ቫይረስ ተከትሎ ፕሪሚየር ሊጉ እስከ ፈረንደቹ ሚያዚያ 3 ድረስ እንዲቋረጥ ከመደረጉ በፊት በሊጉ ያደረገውን የመጨረሻ ጨዋታ በኤምሬትስ የዴቪድ ሞዬሱን ዌስትሃም ዩናይትድን አስተናግዶ ፈረንሣዊው አጥቂ አሌክሳንደር ላካዜት በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል 1ለ0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡ ፡ በደረጃ ሰንጠረዡም ዘጠነኛ ስፍራ ላይ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ በኮረና ቫይረስ መጠቃቱን በይፋ ማስታወቁን ተከትሎ የስፖርት ቤተሰቡ መነጋጋሪ ርዕስ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሀ የአርሰናል የዝውውር ኢላማ ኦርኩን ኮክቹ ማነው? የፌይኖርድ ታዳጊ ኦርኩን ኮክቹ በኤርዲቪዜው እያሳየ ያለውን አስደናቂ ብቃት ተከትሎ በ23 ሚሊዮን ፓውንድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ሊያመራ እንደሚችል በሰፊው በመነገር ላይ ነው፡፡ የስፖርትስ ሜይል ዘገባ የ19 አመቱ ታዳጊ ከመድፈኞቹ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት ይፋ አድርጓል፡፡ የግሮኒገን ወጣት አካዳሚ ትሩፋት የሆነው ተጨዋች በ2014 ፌይናርድን ከተቀላቀለ በኋላ እድገት ማሳየቱን አላቆመም፡፡ ለደች ኃያሉ ክለብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሲያደርግ ገና የ18 አመት ታዳጊ የነበረ ሲሆን በመስከረም 2018 በሀገሪቱ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ላይ ነበር መጫወት የቻለው፡፡ ባለፈው አመትም በኤርዲቪዚዬው የመጀመሪያ ጨዋታው ኳስ እና መረብን ማገናኘት ችሏል፡፡ ኮክቹ የደች ወጣት ብሔራዊ ቡደንን ወክሎ የተጫወተ ሲሆን አሁን ላይ ግን የቱርክ ከ21 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን መለያ በመልበስ በመጫወት ላይ ነው፡፡ ቱርክ የባለፈው አመት እንግሊዝን በገጠመችበት ጨዋታ ላይ ነበር የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው፡፡ ምን አይነት ተጨዋች ነው? ኮክቹ ለአይን የሚማርክ አጨዋወት ያለው የአጥቂ አማካይ ተጨዋች ነው፡ ፡ በመጨረሻዎቹ የተቃራኒ ቡድን ሜዳ ላይ ጫና ፈጥሮ መጫወት ይችላል፡፡ የድሪብሊንግ ችሎታውም የላቀ ነው፡፡ በሚሰጣቸው የተሳኩ ፓሶችም ይታወቃል፡፡ ከረጅም ርቀትም ጎል የማስቆጠር ብቃት አለው፡፡ ለ10 ቁጥር ሚና የተመቸ ተጨዋችም ነው፡፡ አሁን ላይ ይህ ቦታ በሜሱት ኦዚል ተሸፍኖ ይገኛል፡፡ በ2018/19 በኤርዲቪዚዬው ዋናውን ቡድን ሰብሮ ከገባ በኋላ በ11 ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን አስቆጥሮ ሁለት ለጎል የሚሆን ኳስ አቀብሏል፡፡ በዚህም አመትም ተጨማሪ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ በ22 የሊግ ጨዋታዎችም አራት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል፡፡ በእርግጥ ፌይኖርድ በዚህ አመት በዩሮፓ ሊግ አስቸጋሪ ጉዞ አድርጓል፡፡ የምድቡ ግርጌ በመሆን ነበር ያጠናቀቀው ፡፡ ኮክቹ ግን በዚህ መድረክ ሁለት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ለአርሰናል ጥሩ የሚባል ዜና ነው፡፡ መድፈኞቹ አሁን ላይ በሊጉ ዘጠነኛ ስፍራ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ በቀጣይ የውድድር ዘመን ቢያንስ በዩሮፓ ሊጉ የሚያሳትፈውን ቦታ ለማግኘት በመታገል ላይ ነው፡፡ በእርግጥ በቅርቡም ሆነ ቆየት ብሎ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚመለሱበት እድል ይኖራል፡፡ አጨዋወቱ ከማን ጋር ይመሳሰላል? በእርግጥ አጨዋወቱ ከኦዚል ጋር ተቀራራቢ ቢሆንም ለማነፃፀር ምቹ የሚሆነው ግን ከቀድሞ የክለቡ አማካይ ሳንቲ ካዞርላ ጋር ነው፡፡ በፊት እግሩ መጫወቱ፣ ወሳኝ የሆኑ እና ቁልፍ ኳሶችን ማቀበል መቻሉ እና ክፍተት ሲያገኝ ከርቀት ሙከራዎችን ማድረጉ ያመሳስለዋል፡፡ ምናልባት ኮክቹ በመከላከሉ ላይ ያለውን ድክመት ማሻሻል ይኖርበታል፡፡ በተረፈ ግን ስፔናዊው ትቶት የሄደውን ቦታ የመሸፈን አቅም ይኖረዋል፡፡ በየትኛው ቦታ ቢጫወት ብቁ ይሆናል? አብዛኛዎቹ የአርሰናል አማካዮች ክለቡን ሊለቁ እንደሚችሉ በመነገር ላይ ነው፡፡ ምናልባትም ይህ ለተስፈኛው ታዳጊ ጥሩ ዜና ሊሆን ይችላል፡፡ ተፈጥሮአዊ የሆነ የማጥቃት ብቃቱን ተጠቅሞ መድፈኞቹ ያለባቸውን የፈጣሪ ተጨዋቾች ችግር ሊፈታ ይችላል፡፡ ከሉካስ ቶሬራ፣ ማቲዮ ጉንዶዚ እና ግራኒት ዣካ ጋር በመሆን የአማካይ ክፍሉን ጥንካሬ ሊመልስ ይችላል፡፡ ለሚካኤል አርቴታ የ4-3-3 አጨዋወትም የተመቸ ነው፡፡ ሁለት አማካዮችን ከኋላ አድርጎ የማጥቃት ባህሪ ያላቸው ተጨዋቾችንም የመጠቀም ባህሪ ያለው አጨዋወትን ይከተላል፡፡ በዚህም ምክንያት የመሀል አጥቂ ስፍራ ተጨዋቾች ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ አርኩን ኮክቹ የትውልድ ቦታ፤ ሀርለም ኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን፤ ቱርክ ከ21 አመት በታች ክለብ፤ ፌይኖርድ የመጫወቺያ ቦታ፤ የአጥቂ አማካይ የመጀመሪያ ጨዋታው ፤2018 የተጫወታቸው ጨዋታዎች ብዛት ፤38 አጠቃላይ ጎሎች፤ 5 አጠቃላይ ያቀበላቸው ጎል የሚሆኑ ኳሶች ፤10 ሀ